Skip to main content

የማበረታቻ ሽልማት ለቀጣይ ስኬት የሚያነሳሳቸው መሆኑን በሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት የስመዘገቡ የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ገለጹ!
ተማሪዎቹ ይህንንም የገለጹት በዛሬው ዕለት በተካሄዳው የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ሀገር አቀፍ ፈተና ከስፈተናቸው 112 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ማሳለፍ በመቻሉ በተሰናዳው የተማሪዎች የምስጋናና የማበረታቻ ሽልማት ላይ ነው።
ተማሪዎቹም በትምህርት ቤቱ ቆይታቸው የዞኑ አስተዳደር ፣የትምህርት አመራሩ ፣የስልማ አባላት ለደረጉላቸው ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲሁም የወላጅና የመምህራኑ የቅርብ ክትትልና የመማር ማስተማር ምቹነት ለገኙት ውጤት የላቀ አበርክቶ መሆኑን በማንሳት ለዚህ ደረጃ እንዲደርሱ ለደረጉ አካላት ሁሉ አመስግነዋል።
የስልጤ ኮሙኒኬሽን በማበረታቸውና በሽኝት መርሃ ግብሩ ካነጋገርናቸው ተማሪዎች በ2015 ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ተማሪ አ/ረህማን ሹኩር ፣ማዊያ አብዲ እና ሰለስቢል እንዳሉት የተደረገልን ሽኝት በቀጣይ ለዩኒቨርስቲ ቆይታችን ስንቅና በቀጣይ በዞኑ ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚፈተኑ ተማሪዎች ጠንክረው ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲጥሩ ያነሳሳል ብለዋል።
Image