admin
Mon, 01/06/2025 - 17:57
በሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።
ወራቤ፣ ህዳር 7/2017 (ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን)
በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በሚገኘው ሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ለውጤቱ መመዝገብ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የማበረታቻ ሽልማትና የምስጋና መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
መርሃ ግብሩ በይፋ ያስጀመሩት የስልጤ ዞን ዋና አኣተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ የሀይረንዚ መመስረት በሁሉም የዞኑ ትምህርት ቤቶች የውድድር መንፈስ እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል።
ሀይረንዚ ለዞኑ ትምህርት መነቃቃት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ያነሱት አቶ ዘይኔ ጅምሩን ይበልጥ በማጠናከር የትምህርቱን ዘርፍ ጉድለቶች መሙላት ይገባል ብለዋል።
ሀይረንዚ በየተኛውም መልኩ የስልጤን ህዝብ ስም የሚያስጠራ ተቋም መሆኑን በመግለጽ ትምህርት ቤቱንና ስልማን ማጠናከር ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው አንስተዋል።
የስልጤ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሸምሴ ኑሪ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ተማሪዎች በትምህርታቸው ከመበርታት ባሻገር ለስልማ መጠናከር የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በሽልማትና የምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጀማል ረዲ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶ/ር መሐመድ ሽኩር፣ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ዋና ሀላፊ ወ/ሮ ነዒማ ሙኒር፣ የሙለጌ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሃጂ ሙስጠፋ አወል፣ የስልማ የአዲስ አበባ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሃጂ ሁሴን ላለምዳ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሙሐመድ ኸሊል ወራቄ፣ የስልማ ስራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ቀድሩ አብደላ፣ የስልማ ስራ አመራር ቦርድ አባል ወ/ሮ አለይካ ሽኩር፣ የስልጤ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ አባል አቶ መሐመድ የሱፍ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
Image
