Skip to main content

                                                                 የተቋሙ ዳራ

የዞኑን የትምህርት ሽፋን ለማሳደግና ጥራቱን ለማሻሻልና ግንባር ቀደም የሆኑ ሞዴል ት/ቤቶችን ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ታቅዶ የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤትን በማቋቋም ወደ ተግባር የተገባ ነበር፡፡ ዞኑና ልማት ማህበሩ በቅንጅት ብቃት ያለው ሀገር ተረካቢ እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና ስርጸት በሀገርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ለማፍራት እንዲሁም ዞኑ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ት/ቤቶች በመማር ላይ ባሉ ተማሪዎች መካካል ጤናማ የሆነ የውድድር፣ የመማርና የመመራመር መንፈስ እንዲፈጠር ታስቦ በ2007 ዓ.ም የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርት ጀምሯል፡፡ በመሆኑም በ2007 የትምህርት ዘመን ዞኑና ልማት ማህበሩ በወሰደዉ ቆራጥ አቋም ከሁሉም ወረዳዎችና ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ተማሪዎችን በመመልመል የመኝታ ፣ የምግብ ፣ የህክምና እና ሌሎችንም ወጪዎችን በመሸፈን የመማር ማስተማሩን ስራ አሃዱ ብሎ ጀምሯል፡፡ ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ 04 ዙር 10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የስፈተነ ሲሆን 5 ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አስፈትኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ት/ቤቱ 480 ተማሪዎች፣ 29 መምህራን፣ 3 ር/መ/ራንና 12 የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በመያዝ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ት/ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2014 ዉጤት በተደረገዉ ማትግያ እንደ ሀገር 10ኛ ደረጃ በማዉጣት ከሀገሪቱ ጠቅለይ ሚንስተር ሽልማት ተቀብሎዋል እንዲሁም በ2015 ዉጤት 100 % በማሳለፍ እንደ ሀገር 4ኛ ደረጃ መያዝ ችሎዋል፡፡