admin
Mon, 01/06/2025 - 17:07
የወራቤ ከተማ አስተዳደር ለሀይራንዚ ርዕሰ መምህር የ300 ካሬ ሜትር መኖሪያ ቦታ በስጦታ አበረከተ።
ወራቤ ፣ህዳር 23/2016 ፣ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን
ስጦታው የተበረከተው በ2015 በሃገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ሙሉ ተማሪዎቹን አስፈትኖ ላሳለፈው የሀይራንዚ ትምህርት ቤት የማበረታቻ ሽልማት በተሰጠበት ወቅት ነው።
የወራቤ ከተማ አስተዳደር በከንቲባው አቶ ያሲን ከሊል አማካኝነት ለሀይራንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ለአብዱልመጅድ ኑረዲን የ300 ካሬ ሜትር መሬት በስጦታ ተበርክቶለታል።
የወራቤ ከንቲባ ከንቲባ አቶ ያሲን ከሊል ርዕሰ መምህር አብዱልመጅድ ኑረዲን ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ለትምህርት ቤቱ ስኬት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ተቋሙን ውጤታማ ማድረግ የቻለ ታታሪ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን የስራ ባልደረቦቹን አስተባብሮ የሚያሰራ ትጉህ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
የሀይራንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአፍሪካ ደረጃ የልህቀት ተቋም እንዲሆን የስልጤ ልማት ማህበር እየሰራ ስለመሆኑም ተገልጿል።
ከተማ አስተዳደሩ ይህን ስጦታ ለጊዜው ይስጥ እንጂ በቀጣይም አስፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
መሬቱን ከተማ አስተዳደሩ የሰጠ ሲሆን ባለሀብቶች ደግሞ ሙሉ የግንባታ ወጪውን፣ ከነሙሉ ቁሳቁሱ እንችላለን ብለዋል።
በተመሳሳይ ስጦታ የስልጤ ልማት መህበር የ50 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቶለታል።
በተጨማሪም ለሀይራንዚ ትምህርት ቤት መምህራን ለያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ስጦታ የስልጤ ልማት ማህበር አበርክቷል።
Image
