admin
Mon, 01/06/2025 - 17:09
በስልጤ ዞን በሃገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የሀይራንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና መምህራን የእውቅና መረሃ ግብር ተካሄዳ።
ወራቤ ፣ህዳር 23/2015 ፣ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን
የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ሀገር አቀፍ ፈተና ከስፈተናቸው 112 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ማሳለፍ ከቻሉ አምስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ ስልመሆኑ ተገልጿል።
ለዚህም በተሰናዳው የምስጋናና የማበረታቻ ሽልማት ለተማሪዎች እና መምህራንና ለውጤቱ መምጣት ጉልህ አስተዋጽኦ ለበረከቱ ግለሰቦች የገንዘብ፣ የቁሳቁስና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።
የት/ት ቤቱን ርዕሰ መምህሩን ጨምሮ በየ ደረጃው ለሚገኙ መምህራን ለእያንዳንዳቸው ከ10 ሺህ እስከ 50 ሺህ በማበርከት አበረታተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የስልማ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሊ ከድር የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ2007 ጀምሮ በስልጤ ልማት ማህበር ከቋቋመ ጀምሮ በ10ኛ እና በ12ኛ ብሄራዊ ፈተናዎች ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
ዋና አስተዳደሪው አያይዘው ስልጤ ዞን ከፍ ብሎ እንዲጠራ ላደረጋቹሁ ባለድርሻ አካላትና የልማት ማህበሩ አባላት በመሉ በዞኑ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።ልማት ማህበሩ በዞኑ ብሎም በሀገርና አለም አቀፍ ብቁና ተወዳደሪ የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት እያታታረ ይገኛልም ብለዋል።
በቀጣይ በት/ቤቱ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ቀጣይነት ባለው መልኩ መሄድ እንዲችል የልማት ማህበሩ አባላት እና የኮርፖሬት አካላትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።
የሀይረንዚ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት በ2007 የት/ት ዘመን በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ 120 የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል በ12 መምህራን እና በ15 የአስተዳደር እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በመያዝ የመማር ማስተማር ስራውን እንደጀመረ የተናገሩት የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሹክራላ አወል ናቸው።
በአሁኑ ሰዓት በ2015 ትምህርት ዘመን በ30 መምህራን በ46 የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በመያዝ 452 ተማሪዎችን ከ9ኛ -12ኛ ክፍል ደረጃ በለው ሙሉ የትምህርት፣ የምግብ፣ የህክምና፣ እና የመኝታ ወጪ ችሎ እያስተማረ ይገኛል ብለዋል፡፡
ተማሪዎቹ ገና ከጅምሩ ሞዴል ሆነው እንዲወጡ ማድረግ ያለውን ፋይዳ ግምት ውስጥ ያስገባ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያለ ተቋም ነው ያሉት አቶ ሹክራላ ተማሪዎቹ በስነ-ምግባርና በውጤታቸው ዓርዓያ እየሆኑ እንዲሄዱ በተለይ በተማሪዎች መካከል ሰላማዊ የሆና የዉድድርና የመደጋገፍ መንፈስ እንዲኖር የማድረግ ስራም እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ 04 ዙር 10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የስፈተነ ሲሆን 5 ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አስፈትኗል፡፡ ት/ቤቱ ብሄራዊ ፈተና ባስፈተነዉ በሁሉም ዙር እንደ ሀገር ከደረጃና ከሽልማት ተለይቶ አያዉቅም ብቻም ሳይሆን አሁን በሀገር ደረጃ ምርጥ ት/ቤቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል ሲሉም ኃላፊው አስረድተዋል።
በ2015 የት/ት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተናቸዉን 112 ተማሪዎች 100% በማሳለፍ እንደ ሀገር ከአምስት ት/ቤቶች አንዱና በደረጃም 4ኛ ደረጃ በማዉጣት መላ ህዝባችንና የልማት ማህበራችን ከፍታ የሳየበት ዓመት መሆኑን በማንሳት የእንኳን ደስ አለችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
የልማት ማህበሩ አባለት በቀጣይ ይበልጥ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታዎች ከዞኑ መንግስት ጋር መክረዋል። ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ባለሀብቶችና ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው ልማት ማህበሩ ከተቋቋመለት ዓላማ አንጻር ስኬቶች ቢኖሩም ከህዝቡ ፍላጎት ቡዙ የሚቀሩ የልማት ሂደቶች መኖራቸውን ተናግራዋል። ለዚህም መላው የስልጤ ህዝብና አጋር አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የማበረታቻ ሽልማት የተበረከተላቸው ተማሪዎችና መምህራን በሰጡት አስተያየት ሽልማቱ የበለጠ የሚያነሳሳቸውና የሚያሰራቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ተወላጅ ባለሃብቶችና የልማት ማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ከ100 ሺህ እስከ 500ሺህ በማሰባሰብ ለተማሪዎቹ የገንዘብና የላፕቶፕ ኮምፒውተርን ጨምሮ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ ሽልማቶችን ሰጥተዋል።
በመርሐ ግብሩ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ እና የስልማ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሊ ከድርን ጨምሮ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ቀድሩ አብደላ ፣የዞኑ ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አለይካ ሹኩር ፣ የልማት ማህበሩ ቦርድ አመራሮችና የማህበሩ አባላት ፣ የትምህርት ዘርፍ አካላትና አመራሮች እንዲሁም መምህራን፣ ተሸላሚ ተማሪዎችና ወላጆች ተገኝተዋል።
Image
