admin
Mon, 01/20/2025 - 11:38
በስልጤ ዞን ሀይረንዚ ልዩ 2ተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት በ2008ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከወሰዱ 98 ተማሪዎች ውስጥ 75ቱ 4 ነጥብ ማስመዝገባቸው ተጠቆመ።
በሚያስተምሩት የት/ት ዓይነት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መምህራንና በት/ቤቱ 10ኛ ክፍል ማትሪክ ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች በተዘጋጀው የሽልማትና የዕውቅና ፕሮግራም ወቅት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መዘረዲን ሁሴን 4 ነጥብ ካስመዘገቡት 75 ተማሪዎች ውስጥ 42ቱ ተማሪዎች በሁሉም የት/ት ዓይነቶች ቀጥታ "A" ያመጡ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ከተማሪዎች በተጨማሪ የባለድርሻ አካላት ሚናም የላቀ ድርሻ እንደነበረው ጠቁመዋል። በዝግጅቱ ወቅት የስልጤ ልማት ማህበር ስራስኪያጅ አቶ ናስር መሀመድ በበኩላቸው የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስልማ ካከናወናቸው በርካታ ተግባራት ውስጥ የሚጠቀስ ሲሆን በሁሉም ተግባራት ዙሪያ ከማህበሩ ጎን በመሆን ድጋፋቸውን ላበረከቱ አካላት የምስጋና መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በቀጣይ ለሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችም ሁሉም አካላት የልማት ማህበሩ አጋር ሊሆኑ እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።በመጨረሻም አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተለያዩ የዞን ከፍተኛ የአመራር አካላት በኩል የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
Image
