admin
Mon, 01/20/2025 - 16:24
የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አሊ ከድር እና የስልጤ ዞን የመንግስት ዋና ተጣሪ አቶ ቀድሩ አብደለ የሀይራንዚ ልዩ 2ኛ ደረጀ ትምህርት ቤት በመገኘት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን አበረታቱ።
ጥቅምት 17/2014 ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን
ከጥቅምት 29/ 2014 ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስማልክቶ አቶ አሊ ከድር እና አቶ ቀድሩ አብደለ ሀይራንዚ ልዩ 2ኛ ደረጀ ት/ቤት በመገኘት ተማሪዎችን በማበራታታትና በቅድመ ዝግጅት ላይ የተኮረ አጠር ያለ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አሊ ከድር እንዳሉት ተማሪዎች ሳይማር የስተማረቸውን ማህበረሰብ ትልቅ ሀላፊነትና የሀገራችን ተስፋ መሆናቸውን በመገንዘብ ቀጣይ በሚሰጠው ፈተና በተረጋጋ መንፈስ ከወዲሁ ዝግጁ ሆነው የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ማድረግ እንዲችሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ትምህርት ቤቱ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከሀገር አቀፍ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወደዳሪ ዜጎችን ለማፍራት በተነሳው ልክ ስልጤ ልማት ማህበር(ስልማ) አላማውን ያሰካ መሆኑን ጠቁመዋል።
አቶ ቀድሩ አብደለ በበኩላቸው የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጀ ተማሪዎች የስልጤ ብቻ ሳትሆኑ የሀገራችን ብሩህ ተስፋ ስለሆናችሁ በቀጣይ የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ላይ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
በፕሮግራሙ ተሳታፊ የነበሩ ተማሪዎች በቅድመ ዝግጅት ሂደት ላይ አስተያየታቸውን እደሰጡት በየ ጊዜው ት/ቤቱ ላይ በመገኘት ከጎናቸው ሆነው ላደረጉላቸው ማበረታቻ አመስግነው ዘንድሮ በቀጣይ ለሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ኮቪድ የፈጠረባቸውን ከፍተኛ ተጽዕኖ በመግለጽ ት/ቤቱ በልዩነት እርስ በርስ በመደጋገፍና በግሩፕ ጥያቄዎችን በመስራት ዝግጅት ማድረጋቸውን አመላክተዋል።
በቀጣይ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጀ ትምህርት ቤት 84 ወንድ ፣ 22 ሴት ፣ በድምሩ 106 ተፈታኝ ተማሪዎችን ዝግጅት ማድረጋቸውን የት/ት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አ/መጂድ ኑረዲን ገልፀዋል።
Image
