Skip to main content
የሀይራንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምርጥ ተሞክሮን ለሌሎች በዞኑ ለሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስፋት ያለመ የውይይት መድረክ ተካሄዷል!
ታህሳስ 10/2016 ስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን
መድረኩ በስልጤ ዞን ባህል አዳራሽ እየተካሄደ ሲሆን በመድረኩም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን ፣የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
መድረኩን በንግግር የጂሩት የስልጠ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሹክራላ አወል በተለመደው ልምድ የትምህርት ጥራትን ለማረጋጋጥ አይቻልም ያሉት ኃላፊው ስለሆነም አድስ መንገድ በማመቻቸት የተማሪዎችን ውጤት ከፍ እንዲል ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
በተጨማሪም ውጤት ለማምጣት ችግሮች ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ ይጠበቃል ያሉት ኃላፊው ሁሉም በየ አቅሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ትግል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመድረኩ የሀይራንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የስነ ምግባር እና ውጤት የማሻሻል መልካም ተሞክሮ የየዘ ሰነድ በትምህርት ቤቱ ምክትል ር/መምህር በአቶ አብደላ መሀመድ ቀርቧል።
ለስራው ራሳችን ካላዘጋጀን ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት አይቻልም ያሉት አቶ ሹክራላ ሀይራንዚ ላይ ተቀምሮ የቀረበውን ልምድ ወስዶ በስራ ላይ ማዋል ይጠበቅብናል ብለዋል።
Image