Skip to main content
የሀይረንዚ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ህንጻ የዲዛይንና የሳይት ርክክብ ተደረገ።
ወራቤ፣ ህዳር 7/2017 (ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን)
በሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች መኖሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሴት ተማሪዎች ማደሪያ ለሚገነባው ዘመናዊ ህንጻ የዲዛይንና የሳይት ርክክብር ተደርጓል።
የማደሪያ ህንጻው በስልማ አባላት ባለሃብቶች ትብብር የሚገነባ ሲሆን የግንባታውን ዲዛይን ጨምሮ የስራውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የባለሃብቶቹ ተወካዮች ለስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪና ለስልጤ ልማት ማህበር የስራ ሀላፊዎች አስረክበዋል።
የህንጻው ግንባታ በቅርቡ ተጀምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅና ይህም በትምህርት ቤቱ ውስጥ የነበረውን የሴት ተማሪዎች ማደሪያ እጥረት እንደሚቀርፍ በመርሃ ግብሩ ተጠቁሟል።
ባለሃብቶቹን ወክለው መልዕክት ያስተላለፉት የሙለጌ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚና ባለቤት ሃጂ ሙስጠፋ አወል የህንጻው ግንባታ ያለ ተጨማሪ ሂደት በፍጥነት እንደሚጀመር አንስተዋል።
ግንባታው ተጠናቆ ላታቀደለት ዓላማ እስኪውል የቅርብ ክትትል እንደሚደረግበትም ሀጂ ሙስጠፋ ተናግረዋል።
የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ባለሀብቶች ለወሰዱት ሀላፊነት አመስግነው ግንባታው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ርክክብ እንደሚደረግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የስልጤ ዞን ዋና አስዳዳሪን ጨምሮ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአሚን ሆስፒታል ባለቤት ዶ/ር መሐመድ ሽኩር፣ የሙለጌ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚና ባለቤት ሃጂ ሙስጠፋ አወል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጀማል ረዲ፣ የአዲስ አበባ የስልማ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሀጂ ሁሴን ላለምዳን ጨምሮ ሌሎች የስልማ፣ የዞንና የወራቤ ከተማ ባለድርሻ አካላት ህንጻው የሚያርፍበትን ቦታ ጎብኝተዋል።
Image