admin
Sat, 01/25/2025 - 19:02
በስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ዘይኔ ብልካ የተመራው ልዑክ የኢትዮጲያ ቤተመዛግብት ቤተ መጻሐፍት የዘርፉ ኃላፊዎች እና በሀገረ-አቀፍ ደረጀ የስነ-ፅሁፍ ዘርፍ ታዋቂ ሰዎች ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ እንዲሁም ጋዜጠኞች በየሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።
በጉብኝቱም እንደዞን በዛሬው ቀን የተጀመረውን "የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጲያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊዎች የተለየዩ አይነት ያላቸው መጻሕፍትን የፃፈው ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ መሀመድ አሊ(ቡርሃን አዲስ)፣ ደራሲና ገዜጠኛ ሁሴን ከድርና ሌሎችም ደራሲያን ለሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ለተማሪዎች የህይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል።
በመርሃ ግብሩ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ዘይኔ ብልካን ጨምሮ ሁሉም እንግዶች ለተማሪዎች የህይወት ልምዳቸውን በማካፈል መምበብ እና መገንዘብ ላይ ያለ ምንም መዘናጋት መጠንከር እንደሚያስፈልጋቸው መልእክት በማስተላለፍ የላይብሪና ቤተ መፀሀፍት እንዲሁም የተማሪዎችን ማደሪያ ዶርም ተዘዙረው ምልከታ አድርገዋል።
Image
