Skip to main content
የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከ12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መልስ በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አደረጉ።
በዞኑ ባሉ ሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የ12 ተኛ ክፍል ተፈተኝ ተማሪዎች በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
ህዳር 2/2014 ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን
የውይይት መድረኩን የመሩት የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዲሌ እንዳሉት አሁን ላይ በዓለም ላይ የግራ ዘመምና ቀኝ ዘመም የፖለቲካ ርዕዮት ፍጭት ውስጥ እየገቡ መምጣታቸውን አብራርተዋል።ይህ ደግሞ በበለፀጉ አገራትና ባለደጉ ሀገራት መካከል ውጥረት እንዲነግስ አድርጓል።
የወራቤ ከተማ አስተዳደር ረዳት የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ኑራ ባሙዱ በበኩላቸው የውይይቱ ዋነኛ ዓላማ ተማሪዎቹ ሀገራዊና ነባራዊ ሁኔታ በወጉ እንዲረዱት ማድረግ፣ በቀጣይ በሚኖራቸው የረፍት ጊዜ በበጎ አድራጎት ስራዎች፣በገጠርም በከተማም የተጀመሩ የልማት ስራዎች በተለይ ከምርት አሰባሰብ ጋር ተያይዞ ቤተሰብን እንዲያግዙ ለመምከር ነው ብለዋል።
ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ሀገራችን ላይ እየተስተዋለ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ለአሉባልታዎች ጆሮ ሳይሰጡ የእረፍት ጊዜያቸውን የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ልማታዊ ስራዎች በመሳተፍ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚገባቸው የመድረኩ የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል።
የስልጤ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በፈተናው ሂደት ላይ ያናገራቸው አንድ አንድ ተማሪዎች እንደተናገሩት ፈተናው ያለምንም ችግር ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን በማንሳት በቀጣይ ባሉን ክፍት ጊዜያት ስለ ሀገራችን በማህበራዊ ሚዲያ በሚነዙ አሉባልታዎች ሳንሸበር ለተጀመረው የብልፅግና ጉዞ አጋዥ ለመሆን ተዘጋጅተናል ብለዋል።
Image