Skip to main content

                                                  የመማር ማስተማር ሂደትን በተመለከተ

በት/ቤቱ የሚማሩ ተማሪዎች በት/ት ቤት ቆይታቸው በቂ እውቀት እና ክህሎት ይዞ እንዲወጡ መምህራን ተማሪ ተኮር አሳታፊ የማስተማር ስነዜደ  በክፍል ውስጥ በመተግበር የሚያስተምሩ ሲሆን በየጊዜው የተለያዩ ጥያቄዎችን በወርክ ሺት መልክ በማዘጋጀት ተማሪዎች እንዲሰሩ በመስጠት ክትትል እና ድጋፍ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡ከዚህም በተጨማሪ  በት/ት ውጤታቸው ዝቅ ያለባቸውን ተማሪዎች መሰረታዊ ችግራቸውን በመለየትና የተለየውን ችግር መሰረት በማድረግ ለተማሪዎች ድጋፍ እየሰጡ መሄድ በመቻላቸው በት/ት ቤቱ በየአመቱ በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ላይ ጭምር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ 

                                          በት/ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገበ ውጤት

ት/ቤቱ በ2008 ለመጀመሪያ ጊዜ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ማስፈተን የቻለ ሲሆን የከፍተኛ ት/ት ተቋም መግቢያ ፈተናንም በ2010 ለመጀመሪያ ጊዜ በማስፈተና እስካን ባለው በ4ዙር  ተማሪዎች ፈተናውን ተፈትነው ወደ ከፍተኛ ት/ት ተቋም መግቢያ ውጤት አስመዝግበው መግባት ችለዋል፡፡

                                            የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት

በት/ት ቤቱ የ10ኛ ክፍል ሲሰጥ በነበረባቸው አመታት ውስጥ ት/ቤቱ ከ2008 እስከ 2011 ድረስ ባሉት 04 አመታት 384 ተማሪዎች ፈተናውን 335 ተማሪዎች 4.00 ነጥብ፣ 34 ተማሪዎች 3.86 እንዲሁም የተቀሩት 16 ተማሪዎች ከ3.29-3.71 ድረስ ያለውን ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡

                          የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በከፍተኛ ት/ት ተቋም መግቢያ ፈተና የተመዘገበ ውጤት (2010-2013 ዓ.ም)

Year 

Recorded Score

Recorded results

Highest scored result

Lowest scored result

600 and above

599 - 500

Below 500

2010

73

25

98

8

0

8

64

24

88

1

1

2

616

468

2011

81

12

93

3

0

3

76

12

88

2

0

2

608

476

2012

68

10

78

27

5

32

40

5

45

1

0

1

650

495

2013

84

22

106

11

02

13

73

20

93

0

0

0

624

522

2014

 

 

93

0

21

55

14

93

0

21

55

14

93

0

2015

 

 

112

3

37

64

8

112

3

37

64

8

112

3

2016

77

27

104

5

36

40

23

104

5

36

40

23

104

5

Total

Total

306

69

684

64

408

164

45

684

64

408

164

45

 

በመሆኑም ት/ቤቱ ብቃት ያለው ሀገር ተረካቢ እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና ስርጸት በሀገርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ማፍራት እና በዞኑ ላሉ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሞዴል እና የተሞክሮ ማዕከል እየሆነ ባለፉት ስድስት ዓመት በርካታ የሚያስደንቅ ተግባራት ተከናዉኖ ዉጤትም ተመዝግቧል፡፡

ት/ቤቱ በሀገር  አቀፍ ደረጃ በ2014 ዉጤት በተደረገዉ ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገቡ ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ ማትግያ እንደ ሀገር 10ኛ ደረጃ በማዉጣት ከሀገሪቱ ጠቅለይ ሚንስተር ሽልማት ተቀብሎዋል፡፡ ት/ቤታችን ሀይራንዚ ልዩ አዳሪ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ተማሪዎች በ2015 የ/ት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ዉጤትና 100% ያስፈተናቸዉን ተማሪዎች በማሳለፍ እንደ ሀገር ከአምስት ት/ቤቶች አንዱና በደረጃም 4ኛ ደረጃ በማዉጣት ህዝባችንና ልማት ማህበራችንን በከፍተኛ ሁኔታ አኩሩቶናል፡፡

ዛሬም ት/ቤታችን ሀይራንዚ ልዩ አዳሪ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ተማሪዎች በ2016 የ/ት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ዉጤትና 100% ያስፈተናቸዉን ተማሪዎች በማሳለፍ እንደ ሀገር የ2017 ዓ.ም ከአራት ምርጥ ት/ቤቶች አንዱ በመሆንበብሄራዊ ተማሪዎች ሽልማት ኢንስትቲዩት በማሸለም ህዝባችንና ልማት ማህበራችንን በከፍተኛ ሁኔታ አኩሩቶናል፡፡