admin
Mon, 01/06/2025 - 16:56
በስልጤ ዞን በሃገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የሀይራንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና መምህራን የእውቅና መረሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።በፕሮግራሙ ጉልህ አስተውፅኦ ላበረከቱ አካላት የሽልማትና ስጦታ እንዲሁም ማበረታቻዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በፕሮግራሙ ጉልህ አስተውፅኦ ላበረከቱ አካላት የሽልማትና ስጦታ እንዲሁም ማበረታቻዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በዞኑ በስልማ አስተባባሪነት ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመው ይህ የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዞኑ ብሎም እንደ ሀገር ብቁና ተወዳዳሪ የሆነ የተማረ ሀይል ከማፍራቱም ባለፈ በአፍሪካ የልህቀት መአከል ለመሆን አንግቦ እየታተረ የሚገኝ ተቋም ነው።
በዛሬው እለት በዚሁ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች በሚሰጠው የእውቅና እና የሽኝት መርሓ-ግብር ላይ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የስልጤ ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሊ ከድር እና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ቀድሩ አብደላ ፣የወረዳና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣የትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ተሸላሚ ተማሪዎችና ወላጆች ፣ከአዲስ አበባና ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የሚኖሩ የስልጤ ባለሀብቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
Image
