admin
Mon, 01/20/2025 - 12:11
እንኳን ደስ ያለን!! እንኳን ደስ ኣላችሁ!! በስልጤ ዞን የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በ2009 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተናቸው 97 ተማሪዎች ውስጥ 94ቱ ተማሪዎች አራት ነጥብ(4) እና 3 ተማሪዎች 3.8 ማምጣት ችለዋል። አራት ነጥብ ካስመዘገቡት ዘጠና አራት ተማሪዎች ውስጥም 88ቱ (ወንድ=77 ሴት=11) በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች A ያመጡ ናቸው። 3.8 ካስመዘገቡት ተማሪዎች ውስጥ ወንድ=3 እና ሴት=0 ድምር=3 ናቸው።በዚህም የስልጤ ልማት ማህበርና የትምህርት ቤቱ የስልጠና ቦርድ ለመላው የዞኑ ማህበረሰብና ለአጋር አካላት የእንኩዋን ደስ ኣላችሁ መልዕክቱን እያስተላለፈ በተለያዩ ዘርፎች በቀጣይ ለሚያከናውናቸው ተግባራትም ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ድጋፋችሁ እንዳይለየን ይላል።
Image
