Skip to main content
የስልጤ ዞን አስተዳደር ከስልጤ ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ለሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም አጠቃላይ ሰራተኞች የእፍጣር መርሃ-ግብር አካሄደዋል!
መጋቢት 17/2017 ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን
በዝግጅቱ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ዘይኔ ብልካ፣ የስልጤ ዞን ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት መህዲያ ቡሴር ፣የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር፣ የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ነስሮ አለሙ፣ የወራቤ ዩኒቨረስቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢንጅነር ተውፊቅ ጀማል፣ የስልማ ስራ አስኪያጅ አቶ ሸምሴ ኑሪን ጨምሮ ሌሎች የዞንና የወረዳና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል።
የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ውጤት ማሳደግ እንዲሁም ትምህርት ቤቱን በልዩ ልዩ ተግባራት ለማገዝ የሚመለከታቸው አካላት በማስተባበር አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ እገዛ ይደረጋል ያሉት የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ዘይኔ ብልካ ተማሪዎች ጡሩ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክራቹ ትምህርታቹህን ተከታታሉ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
የስልጤ ልማት ማህበር ስራ-አስኪያጅ አቶ ሸምሴ ኑሪ በበኩላቸው ኢፍጣሩ እንዲደምቅ ላደረጉና ከፍተኛ ትብብር ላደረጉ ለስልጤ ዞን አስተዳደርና የሪያድ ሆቴል ባለቤት ለሆኑት ለሀጂ አብዱልሃዲ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
በኢፍጣር መርሃ ግብሩ የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ዌብሳይት ያበለፀጉ ሲሆን ጠቀሜታውን አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል በዚህም የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ሀሳብ አስተያት ሰጥተውበታል።
Image