Skip to main content
በሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት የተመዘገበውን ውጤት መነሻ በድረግ የስልጤ ልማት ማህበር ለአባላት ፣ ለደጋፊዎች ፣ ለመላው የስልጤ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል ፡፡
በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ለምትገኙ ለመላው የስልማ አባላት፣ ደጋፊዎች ፣ ለመላው የስልጤ ህዝብ ውጤቱ የጋራችን ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ/ን!!
በ2017 በጀት ዓመት የትምህርት ዘመን የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ አዳሪ ትምህርት ቤት ተፈትነው የነበሩ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ዪኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ ችለናል ፡፡
የሁላችንም ተቋም የሆነው የስልጤ ልማት ማህበር በማህበራዊ ዘርፍ የወራቤ ሆስፒታል ፣ በተለያዩ ወረዳዎች ቅድመ አንደኛ ትምህርትና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለህዝብና ለመንግስት በማስረከብ ህዝባዊ አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በተመሳሳይ ልማት ማህበሩ የስልጤን ህዝብ ለማሻገር ሩቅ ዓሊሞ በ2007 በጀት ዓመት የመማር ማስተማር ስራውን የጀመረው የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤት ዛሬም እንደ ትላንቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ቀጥሏል ፡፡
የተኛውም ልማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው !! የህዝብ ተቋም የሆነው የስልጤ ልማት ማህበር /ስልማ / አማካኝነት የሚመጡ ውጤቶችም ይሁን ውድቀቶች ደረጃው ይለያይ እንጂ የጋራችን ነው ፡፡
አሁን ላይ ስልማ የሁሉን የተባበረ ክንድና ድጋፍ ይፈልጋል ፡፡
በየዓመቱ በሚያስመዘግበው ውጤት ውስጣችን በሃሴት የሚሞላበት ፣ የምንመካበት የሀይረንዚ ትምህርት ቤት ራሱ በብዙ ጉድለቶች ታጅቦ ውጤት የሚያስመዘግበው ስለሆነም የሁላችን ድጋፍ ይፈልጋል ፡፡
ስልማ የጀመረውን ለመጨረስና አዳዲስና ያሉትን አጠናክሮ ለማስቀጠል በምንችለው ሁሉ ማለትም ዓመታዊ የአባላት ክፍያ በመክፈል ፣ በማስተባበር ፣ በምንገኝበት ሁሉ ልማት ማህበሩን በገንዘብ ፣ በሃሳብ ፣ በዕውቀት ፣ ማህበረሰቡን በማንቃት የበኩላቹን እንድትወጡ ልማት ማህበራችሁ በአክብሮት ይጠይቃል ፡፡
ለሀይረንዚ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ውጤት መመዝገብ ድጋፍ ስታደርጉ የነበራችሁ የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ እስታፍ ፣ ለስልጤ ዞን አስተዳደርና አመራሮች ፣ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ድጋፍ ስታደርጉ የነበራችሁ ሁሉ ስልጤ ልማት ማህበር ከልብ ያመሰግናል ፡፡
በድጋሚ እንኳን ደስ አላች /ን // ይላል የስልጤ ልማት ማህበር !!
መስከረም 05 ቀን 2018 ወራቤ !!
Image