Skip to main content
የሀይረንዚ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት 564 ሆኖ መመዝገቡን የትምህርት ቤቱ ዋና ርዕሰ መምህር አቶ አብድልመጂድ ኑረዲን ገለፁ ፡፡
ትምህርት ቤቱ ያስፈተናቸው ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውን አያይዞ ገልፀዋል ፡፡
በስልጤ ልማት ማህበር የሀይረንዚ ልዪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ አብድመጂድ ኑረዲን እንደገለፁት በ2017 በጀት አመት ትምህርት ቤቱ የስፈተናቸው 105 ተማሪዎች በሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማምጣት መቻላቸውን ገልፀዋል ፡፡
አቶ አብድልመጂድ አያይዘው ከተፈተኑት ተማሪዎች የተማሪ ፍርደውስ አህመድ 564 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ በትምህርት ቤቱ መመዝገብ መቻሉን ገልፀው ከተፈተኑት ተማሪዎች 28 ተማሪዎች ከ500 በላይ የሆነ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል ፡፡
ለዚህ ውጤት መመዝገብ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ እስታፍ ፣ የስልጤ ልማት ማህበር ፣ የስልጤ ዞን አስተዳደር ፣ የዞኑ ትምህርት መመሪያ እንዲሁም በሀገር ውስጥና ከሀገር ወጭ የሚገኙ የልማት ማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች በአጠቃላይ ድጋፍ ላደረጋቹልን ሁሉ በትምህርት ቤቱ ምስጋናቸውን በማቅረብ አሁን ላይ የተገኘው ውጤት በቀጣይ የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳና የሚያመላክተን በመሆኑ ትምህርት ቤቱ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እያረጋገጥኩ አሁን የተመዘገበው ውጤቱ የጋራችን ነውና እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ፡፡
Image