Skip to main content
የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጀ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2017 የትምህርት ዘማን በሃገር አቀፍ ደረጀ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ለውጤት ላበቁ መምህራን የማበረታቻና የእውቅና መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል ።
በመርሃ ግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የስልጤ ዞን ዋና አስተደዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ዞኑ ለትምህርት ልማት ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከ280 ሺህ በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አቶ ዘይኔ አያይዘው ‎የትምህርት ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የዞኑ ተወላጅ ባለሃብቶችና ማህበረሰቡን በማስተባበር ከ330 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን አንስተዋል።
‎በዞኑ የሚገኘው ሃይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተከታታይ አመታት ያስመዘገበው የተማሪዎች ውጤት በጋራ መስራት ከተቻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል አንድ ማሳያ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።
‎ይህንን ውጤታማነት በሁሉም የዞኑ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ለማድረግና ሂደቱ ቀጣይነት እንዲኖረው መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።
‎የሃይረንዚ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ከራሳቸው አልፈው ሀገራቸውን ለመጥቀም የሚችሉ ተማሪዎችን በመፍራት ለይ መሆኑን ገልጸዋል ።
‎ዋና አስተዳዳሪው አክለውም በ2017 የትምህርት ዘመን ውጤት አምጥተው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለሚገቡ ተማሪዎች መልእክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን ትምህርት የእድሜ ልክ ጉዞ እንደመሆኑ ለዚህ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸውም መክረዋል።
ትምህርት የልማቶች ልማት ነው ያሉት ዋና አስተዳደሪው አቶ ዘይኔ ብልካ ሃይራንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጠንክረን ከሰራን ከፍተኛ ውጤት ማምጣትን ለአብነት የያንበት ነው ብልዋል ።
የስልጤ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚ አቶ ሸምሴ ኑሪ የእንኳን ደህና መጣቹሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የስልጤ ልማት ማህበር ከተመሠረተበት ግንባር ቀደም ዓላማዎች አንዱ በማህበራዊ ዘርፍ የሚያደረገው እንቅስቃሴ ተጠቃሽ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከዚህም ውስጥ አንዱ በትምህርት ዘርፍ ብቁና ተወዳደሪ ሀገር የሚያስጠራ ትውልድ ለማፍራት አንግቦ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ለዚህ አንዱ ማሳያ የሀይራንዚ ትምህርት ቤት ማሳያ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሸምሴ ከ2007 ጀምሮ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎችን በማፍራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
ሀይረንዚ አይነት ትምህርት ቤት ለመስፋፋት የስልጤ ልማት ማህበር ከአባላት መዋጮ በተጨማሪ በሌሎች ገቢ ማስገኛ አማራጮች አሁንም ጠንክሮ መስራትን ይጠይቃል ብለዋል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ፣የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ መህዲያ ቡሴር ፣የወራቤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢንጅነር ቶፊቅ ጀማልን ፣የፓርላማ ህዝብ ተወካዮችና የአሚን ሆስፒታል በባለቤት ዶ/ር መሀመድ ሹኩርን ጨምሮ የፌዴራል ፣የክልልና የዞን የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ፣የወረዳና ከተማ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
Image