ራዕይ
ትምህርት ቤቱ በመልካም ሥነ-ምግባራቸውና በላቀ የትምህርት ውጤታቸው በአገር ደረጃ ታዋቂ የሆኑ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ከፍተኛ አስተዋጾ የሚያበረክቱ ተማሪዎች የሚፈልቁበት ተቋም ሆኖ ማየት ነው፡፡
ተልእኮ
ማራኪና ምቹ የትምህርት አካባቢ በመፍጠር፣ የመማር ማስተማር ሥራ ዘመናዊና ተማሪ ተኮር በማድረግ፣ ስትራቴጂክና ሳይንሳዊ የትምህርት አመራር በመስጠት፣ መምህራንና ሠራተኞችን በማሠልጠንና የተለያዩ ልምዶችን እንዲቀምሩና እንዲያካፍሉ በማድረግ፣ የተለያዩ የትምህርት ባለሙያዎችንና ድርጅቶችን በትምህርት ቤቱ ሥራ በማሳተፍ፣ የተግባር ትምህርትን በማጠናከር፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የተቃኘና ተማሪዎችን ለእጅግ ከፍተኛ ውጤት የሚያነሳሳ፣ ለፈጠራና ለሥነ ምግባር ለውጥ የሚያዘጋጅ ትምህርትና ስልጠና መስጠት ነው፡፡
እሴቶች
ለጥራት መትጋት
| ሁልጊዜ መማር | በውስን ሀብት ትልቅ ውጤት
| ግልፀኝነትና ተጠያቂነት |
ቅድሚያ ለሰው ሀብት
| የቡድንሥራ ለስኬት
| መከባበርና መደጋገፍ
| አሳታፊነት ናቸው፡፡
|